Just For Laugh

ለፈገግታ…..
የልጅቷ ስልክ ይጠራል………የማታውቀው ቁጥር
ልጅቷ፦ሄሎ!


ከወዲያኛው ጫፍ፦የወንድ ጓደኛ አለሽ?
ልጅቷ፦አዎ!ግን ለምን ጠየቅከኝ?
ከወዲያኛው ጫፍ፦ አንቺ ደደብ!? አባትሽ ነኝ!በዚህ ዕድሜሽ የወንድ ጓደኛ?እኔ ትምህርትሽን እየተማርሽ
ነው ብዬ………ወይ ጉድ! …ቆይ ብቻ ቤት ስትመጪ እንነጋገራለን።
ስልኩን ዘጋው።
……………………………………………………………
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ…ስልኳ ይጠራል…የማታውቀው ቁጥር………
ልጅቷ፦ሄሎ!
ከወዲያኛው ጫፍ፦የወንድ ጓደኛ አለሽ?
ልጅቷ፦ኧረ በፍፁም!
ከወዲያኛው ጫፍ፦ማሬ…አንድም ቀን ታፍሪብኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፤በጣም አዝኜብሻለሁ።
ልጅቷ፦ኧረ…የኔ ፍቅር…የኔ ጌታ …በጣም ይቅርታ! ያ ጀዝባ ሙደ-ገዳዳ ሼባ መስሎኝ እኮ ነው።

ከወዲያኛው ጫፍ፦አሁንም አባትሽ ነኝ!በደንብ ለማረጋገጥ ፈልጌ ነበር።
ማን ጀዝባ ሙደ-ገዳዳ ሼባ እንደሆነ ቤት ስትመጪ እንነጋገራለን!!!
Source Facebook Wondeson Ayalew . 

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x