ፈረንሳይ ለጤና አሰጊ የሆነ ቅጥነትን ልታግድ ነው -France to ban extreme thinness

በፈረንሳይ ቅጥነት ውበት ነው፥፥ ከልክ ያለፈ መገርጣት ግን አሁን በህግ ያስቀጣል::

ፈረንሳይ ከልክ በላይ የሚከሱ የፋሽን ሞዴሎችን አና ሞዴሎችን ከልክ ላለፈ ቅጥነት የሚዳርጉ ድርጅቶችን ልታግድ ነው::

 

 

የፈረንሳይ መንግስት በቅርቡ የሚያፀድቀው ህግ የፋሽን ሞዴሎች ከልክ በላይ እንዲከሱ የሚያደርጉ ድርጅቶች ላይ የ ሰባ ዘጠኝ ሺ ዶላር ቅጣት ይጥላል ፈረንሳይ ይህንን ህግ

ለማውጣት ያስገደደኝ የኣንዳንድ ሞዴሎች ክሳት ለጤና አሰጊ በመሆኑ ነው ትላለች::

ለማሰታወቂያ ስራ ሲባል የረባ ምግብ ሳይበሉ የሚገረጡ(ኣነሮግዚክ) የሚሆኑ ግለሰቦችን የሚያበረታቱ ሁሉ ወዮላቸው ይላል ኣዲሱ የፈረንሳይ ህግ::

እንደ ሮይተርስ ዘገባ በፈረንሳይ ከ 30-40  ሺ ሰዎች ከልክ ባለፈ ቅጥነት (ኣነሮግዚያ) ይጠቃሉ::

ጣልያን ስፔን እና እስራኤል ከልክ ያለፈ ቅጥነትን በህግ ካገዱ አገሮች ውስጥ ይገኙበታል

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x