Happy Valentine’s Day from ethiofidel.com

Happy Valentine’s day to all of you from ethiofidel.com . Here is a poem by the Toronto based poet and writer Semira Aman

★እናፍቅሀለሁ★

እንደ አዕዋፍ ዜማ
ድምፅህን ስሰማ
ጎልተህ በምናቤ
ስትመጣ ባ’ሳቤ
እናፍቅሀለው ደግሜ ደግሜ
የቁም ቅዠቴ ነህ የለሊቱ ህልሜ

IMG_6455

የፍቅርን ወለላ ልቀምስ
ወዳንተ በምኞት ስገሰግስ
ከራሴ አለም ወጥቼ
ካ’ንተው ተጣብቼ
በፍቅር ፍፁም ናውዤ
በመውደድ ሀሳብ ፈዝዤ
እናፍቅሀለው ዛሬም እንደገና
መቼም ባንተ ነገር አንጀቴ አይጠና

ፍቅርህ ኃያል ሆኖ ውበትህም ሲገን
መንፈሴን ሰውሮ ሀሳቤን ሲበትን
ይበለኝ እላለሁ መልሼ መልሼ
የናፍቆትን አምባ ከጉንጬ አብሼ

አስተዋይነትህ ውበትህን አጉልቶ
ፅኑ አፍቃሪነትህ ታየኝ ተለይቶ
የፍቅርህ ቤዛ……………
የጨዋታህ ለዛ……………
ውልብ………ሲልብኝ
እናፍቅሀለው ፍቅር እየጠናብኝ

ቅን አሳቢነትህ……………
ከቶ ማንነትህ………………
ትዝ ባለኝ ጊዜ………………
የያዘኝ አባዜ………………
ስምህን ደጋግሜ እንደሞት ኑዛዜ
አንተን መናፈቅ ነው በቀን አስር ጊዜ።

ሰሚራ አማን

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x